ምሳሌ 20:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዐይንን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሰሙ ጆሮዎች፣ የሚያዩ ዐይኖች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ሠርቷቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፥ ሁለቱን ጌታ ፈጠራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሰማ ጆሮና የሚያይ ዓይን፥ ሁለቱ የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው። |
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍን የፈጠረለት ማነው? ድዳ ወይም ደንቆሮ፥ ዐይኑ እንዲያይ ወይም እንዳያይ የሚያደርግስ ማነው? ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’