ምሳሌ 10:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ጥበብን ይናገራሉ፤ ጠማማ ነገር የምትናገር ምላስ ግን ትቈረጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤ ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፥ የመጥመም ምላስ ግን ትቈረጣለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ የዐመፀኛ ምላስ ግን ይጠፋል። |
እግዚአብሔር ድልን ስለሚያጐናጽፈው ንጉሡ ደስ ይለዋል፤ በእግዚአብሔር ስም የሚምሉ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሐሰተኞች አንደበት ግን ይዘጋል።