ምሳሌ 1:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው በሚበዛበት መንገድ ትጮኻለች፤ በከተማው መግቢያ የሕዝብ መሰብሰቢያ ላይ ንግግርዋን ታሰማለች። እንዲህም ትላለች፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዉካታ በበዛባቸው ጐዳናዎች ላይ ትጮኻለች፤ በከተማዪቱም መግቢያ በር ላይ እንዲህ ትላለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግርግር ባለበት አደባባይ ትጣራለች፥ በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግንብ ድምድማት ትሰብካለች፥ በኀያላን በሮች ታገለግላለች። በከተማ በሮች በድፍረት እንዲህ ትላለች፦ |
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለሰው ሁሉ በግልጥ ተናገርኩ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኲራብም ሆነ በቤተ መቅደስ፥ ዘወትር አስተማርኩ፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም፤