ፊልጵስዩስ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትሕትና ቍጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራስ ወዳድነት ወይም ከትምክሕት የተነሣ አንድም ነገር አታድርጉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በትሕትና ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንደሚሻል አድርጎ ይቁጠር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ |
ጽድቅን አግኝቶ ወደ ቤቱ የተመለሰው ይህ ቀራጭ ነው እንጂ ፈሪሳዊው አይደለም እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።”
እናንተ አሁንም ገና ሥጋውያን ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ስለምትቀናኑና ስለምትከራከሩ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? የምትሠሩትስ እንደ ተራ ሰው አይደለምን?
እኔ ወደዚያ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት ልትሆኑ እንደምፈልገው ሳትሆኑ፥ እኔም እናንተ እንደምትፈልጉት ሳልሆን እንገናኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ፤ እንዲሁም በእናንተ ዘንድ ጥል፥ ቅናት፥ ቊጣ፥ ራስ ወዳድነት፥ የሰው ስም ማጥፋት፥ ሐሜት፥ ትዕቢትና ሁከት ይኖሩ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን ስለ ቃላት የመከራከርና የመጨቃጨቅ ክፉ ምኞት አድሮበታል፤ ይህም የሚያስከትለው ቅንአትን፥ ጠብን፥ ስድብን፥ መጥፎ ጥርጣሬን፥
በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።