ፊልሞና 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጸሎቴ አንተን እያሰብኩ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን በጸሎቴ በማስብህ ጊዜ አምላኬን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጸሎቴ እያሰብኩህ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጌታ በኢየሱስ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለህ ስለ ፍቅርህና ስለ እምነትህ ሰምቼ፥ በጸሎቴ እያሳሰብሁ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታ በኢየሱስ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለህ ስለ ፍቅርህና ስለ እምነትህ ሰምቼ፥ በጸሎቴ እያሳሰብሁ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ |
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።