በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም ወደ እኔ መምጣት ደስ ብሎኛል፤ እናንተ ከእኔ ጋር ባለመገኘታችሁ እነርሱ በእናንተ ምትክ የጐደለኝን አሟልተውልኛል።
ፊልሞና 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንጌል ምክንያት እዚህ ታስሬ ሳለሁ በአንተ ምትክ ሆኖ እንዲያገለግለኝ እርሱ ከእኔ ጋር ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ወንጌል በታሰርሁበት ጊዜ በአንተ ፈንታ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው ፈልጌ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔስ ስለ ወንጌል በገጠመኝ እስራት አንተን ወክሎ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው በፈቅድኩ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ልቤ እንደሚሆን ተቀበለው። እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር፥ |
በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም ወደ እኔ መምጣት ደስ ብሎኛል፤ እናንተ ከእኔ ጋር ባለመገኘታችሁ እነርሱ በእናንተ ምትክ የጐደለኝን አሟልተውልኛል።
አሁን በእስር ቤት ባለሁበት ጊዜና ከመታሰሬም በፊት ለወንጌል እውነት ለመከላከልና እርሱንም ለማጽናት እግዚአብሔር በጸጋው በሰጠኝ ዕድል ሁላችሁም ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ እናንተ ሁልጊዜ በልቤ ናችሁ። ስለዚህም ስለ እናንተ የሚሰማኝ ስሜት ትክክል ነው።
እናንተ በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን ርዳታ እርሱ ለማሟላት ብሎ ስለ ክርስቶስ ሥራ ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለሞት ተቃርቦ ነበር።
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ከሆንኩ ከእኔ ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ ለተወደደው ወንድማችንና የሥራ ጓደኛችን ለሆነው ለፊልሞና፥