ዘኍል 9:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ሰፈራቸውን ለቀው ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በሚወርድበት ቦታ እንደገና ይሰፍሩ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ እስራኤላውያን ጕዟቸውን ይጀምሩ ነበር፤ ደመናው በሚቆምበት ቦታ ደግሞ ይሰፍሩ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በማናቸውም ጊዜ ሲነሣ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም ባረፈበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። |
መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።
መራብና መጠማትም አይደርስባቸውም፤ የሚያቃጥል ነፋስ ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም፤ ይህም የሚሆነው የሚራራላቸው እርሱ የውሃ ምንጭ ወደሚገኝበት ቦታ ስለሚመራቸው ነው።
ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።