ዘኍል 32:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቶቻችንና ልጆቻችን፥ ከብቶቻችንና በጎቻችን፥ በዚህ በገለዓድ ከተሞች ይቈያሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቻችንና ሚስቶቻችን፣ የበግና የፍየል እንዲሁም የከብት መንጎቻችን እዚሁ በገለዓድ ከተሞች ይቀራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻችን ሚስቶቻችንም፥ እንሰሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ |
ብዙ ከብት እንዳላችሁ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እዚህ መቅረት የሚችሉት ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ ናቸው፤ ስለዚህም እነርሱን እኔ በሰጠኋችሁ ከተሞች ወደ ኋላ ትታችሁ ትሄዳላችሁ።
ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቈዩ፤ የጦር ልብስ ለብሰው ለውጊያ የተዘጋጁ ሰዎቻችሁ ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው ዮርዳኖስን ይሻገሩ፤
የሮቤል፥ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነዓን ምድር በሚገኘው በሴሎ ካሉት ከእስራኤላውያን ዘንድ ተነሥተው በሙሴ አማካይነት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተሰጣቸው ምድር ወደ ገለዓድ ተመለሱ።