ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍን የፈጠረለት ማነው? ድዳ ወይም ደንቆሮ፥ ዐይኑ እንዲያይ ወይም እንዳያይ የሚያደርግስ ማነው? ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ዘኍል 22:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ለአህያይቱ የመናገር ችሎታ ስለ ሰጣት በለዓምን “እኔ ምን አደረግሁህ? ሦስት ጊዜ የደበደብከኝ ስለምንድን ነው?” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር የአህያዪቱን አፍ ከፈተ፤ በለዓምንም፣ “እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌህ ነው?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የአህያይቱን አፍ ከፈተ፥ በለዓምንም፦ “ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌህ ነው?” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የአህያዪቱን አፍ ከፈተ፤ በለዓምንም፥ “ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የአህያይቱን አፍ ከፈተ፥ በለዓምንም፦ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው። |
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍን የፈጠረለት ማነው? ድዳ ወይም ደንቆሮ፥ ዐይኑ እንዲያይ ወይም እንዳያይ የሚያደርግስ ማነው? ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?