ማቴዎስ 23:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ዕውሮች መሪዎች! ከምትጠጡትም ሁሉ እንደ ትንኝ ትንሽ የሆነችውን ነገር አጥልላችሁ ትጥላላችሁ፤ እንደ ግመል ትልቅ የሆነውን ነገር ግን ትውጣላችሁ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የታወራችሁ መሪዎች፤ ትንኝን አጥርታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ዕውራን መሪዎች! ትንኝን አጥልላችሁ ታወጣላችሁ ግመልን ግን ትውጣላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ዕውሮች መሪዎች! ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ። |
“እናንተ ዕውሮች መሪዎች! ወዮላችሁ! ‘ሰው በቤተ መቅደስ ቢምል፥ ምንም አይደለም’ ትላላችሁ፤ ‘በቤተ መቅደሱ ወርቅ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል’ ትላላችሁ፤
ከዚህ በኋላ ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ አገረ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ጊዜውም ጠዋት ማለዳ ነበር፤ አይሁድ ለፋሲካ በዓል የሚታረደውን በግ መብላት ስለ ነበረባቸው እንዳይረክሱ በማለት ወደ አገረ ገዢው ግቢ ውስጥ አልገቡም።