La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 22:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለግብር የሚከፈለውን ገንዘብ እስቲ አሳዩኝ!” አላቸው። ስለዚህ እነርሱ አንድ ዲናር አምጥተው አሳዩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለግብር የሚከፈለውን ገንዘብ እስኪ አሳዩኝ።” እነርሱም አንድ ዲናር አመጡለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለግብር የሚከፈለውን ብር አሳዩኝ።” እነርሱም ዲናር አመጡለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የግብሩን ብር አሳዩኝ፤” አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የግብሩን ብር አሳዩኝ አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 22:19
7 Referencias Cruzadas  

ጴጥሮስም “ኧረ ይከፍላል” አላቸው። ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ጴጥሮስ ሆይ! ምን ይመስልሃል? የዚህ ዓለም መንግሥታት ቀረጥና ግብር የሚቀበሉት ከማን ነው? ከልጆቻቸው ነውን ወይስ ከውጪ አገር ሰዎች?” ሲል ጠየቀው።


“ነገር ግን ያ አገልጋይ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ሳለ መቶ ዲናር ያበደረውን የሥራ ጓደኛውን አገኘና አንገቱን አንቆ ይዞ፥ ‘ያበደርኩህን ገንዘብ ክፈለኝ!’ አለው።


እርሱ ለእያንዳንዱ በቀን አንድ ዲናር ሊከፍል ተዋውሎ፥ ሠራተኞችን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ ላካቸው።


ኢየሱስ ግን ክፋታቸውን ዐውቆ፥ “እናንተ ግብዞች! ስለምን ትፈትኑኛላችሁ?


እርሱም፥ “በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፤


እነርሱም ገንዘቡን አመጡለት፤ እርሱም “በዚህ ገንዘብ ላይ ያለው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው፤” አሉት።


ከአራቱ እንስሶች መካከል የመጣ የሚመስል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህ ድምፅ “ግማሽ ኪሎ ያኽል ስንዴ የአንድ ቀን ደመወዝ፥ ለአንድ ኪሎ ተኩል ያኽል ገብስ ለአንድ ቀን ደመወዝ ይሁን፤ ዘይትንና ወይንን ግን አትጒዳ!” ሲል ሰማሁ።