ማርቆስ 2:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበትም ጌታዋ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታዋ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው አላቸው። |
ከዚያም በኋላ “ለመሆኑ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ።
በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ።