ሉቃስ 20:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎች አከራየውና ወደ ሌላ አገር ሄደ፤ ሳይመለስም ብዙ ጊዜ ቈየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎችም አከራየና ወደ ሌላ አገር ሄዶ ብዙ ጊዜ ቈየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ምሳሌ ለሕዝቡ ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ለወይን ጠባቂዎች አከራይቶ ለረጅም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝቡም ይህን ምሳሌ ይመስልላቸው ጀመረ፤ እንዲህም አላቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭመቂያም አስቈፈረ፤ ግንብም ሠራለት፤ ለገባሮችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይመለስም ዘገየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ምሳሌ ለሕዝቡ ይላቸው ጀመር። አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ ለገበሬዎችም አከራይቶ ለብዙ ዘመን ወደ ሌላ አገር ሄደ። |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “በዚያን ጊዜ ወደ መንግሥተ ሰማይ የመግባት ሁኔታ እንዲህ ይሆናል፦ አንድ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ንብረቱን እንዳስረከባቸው ዐይነት ይሆናል።
ወይኑ ባፈራ ጊዜ የወይኑ ተክል ባለቤት ከፍሬው ድርሻውን እንዲቀበልለት አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው፥ ባዶ እጁን ሰደዱት።
“አምላክህ እግዚአብሔር ለየነገድህ በሚሰጠው ምድር በእያንዳንዱ ከተማ ዳኞችና ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ትሾማለህ፤ እነዚህም ሰዎች ለሕዝቡ ያለ አድልዎ መፍረድ ይገባቸዋል፤