ሉቃስ 2:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይገረሙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሶቹ ተገረሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰሙትም ሁሉ አስተዋይነቱንና አመላለሱን ያደንቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። |
ወደ አገሩ ወደ ናዝሬት ከተማ መጥቶ በምኲራቦቻቸው ሕዝብን ያስተምር ነበር፤ የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና ይህን ድንቅ ሥራ ከወዴት አመጣው?
የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ይህን ሲናገር ሰሙት፤ ሕዝቡም ሁሉ በትምህርቱ ይደነቁ ስለ ነበር ፈሩት፤ ስለዚህ እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ዘዴ ይፈልጉ ነበር።
በሰንበት ቀን በምኲራብ ማስተማር ጀመረ፤ ብዙ ሰዎች በዚያ ተገኝተው ይሰሙት ነበር፤ እነርሱም “ይህ ሰው ይህን ሁሉ ነገር ከየት አገኘው? ምን ዐይነት ጥበብ ተሰጥቶታል? እነዚህንስ ተአምራት የሚያደርገው እንዴት ነው?” እያሉ ይደነቁ ነበር።