ሉቃስ 2:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ዮሴፍና ማርያምም በሕጉ መሠረት የተለመደውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስም ተነሣስቶ ወደ መቅደስ መጣ፤ ወላጆቹም እንደ ሕጉ ልማድ ሊያደርጉለት ሕፃኑን ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስም ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደው፤ ዘመዶቹም በሕግ የተጻፈውን ያደርጉለት ዘንድ ሕፃኑን ጌታችን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ በአገቡት ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈስም ወደ መቅደስ ወጣ፤ ወላጆቹም እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕፃኑን ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ፥ |
በሕግ መሠረት፥ የመንጻት ሥርዓት የሚፈጸምበት ጊዜ ደረሰ፤ ስለዚህ ማርያምና ዮሴፍ ሕፃኑን በጌታ ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት ሄዱ።
ዮሴፍና ማርያም በቤተ መቅደስ ባዩት ጊዜ ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜ እናቱ፥ “ልጄ ምነው እንዲህ አደረግኸን? አባትህና እኔ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው።
ያላንዳች ማመንታት ከእነርሱ ጋር እንድሄድም መንፈስ ቅዱስ ነገረኝ፤ እነዚህ ስድስት ወንድሞችም ከእኔ ጋር ነበሩ፤ ከእነርሱም ጋር አብረን ቆርኔሌዎስ ወደ ተባለው ሰው ቤት ገባን።
ከዚህ በኋላ መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ በሁለንተናው የስድብ ስሞች በተጻፉት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ባሉት በቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች አንዲት ሴት አየሁ።