በመንገድ ላይ ሳሉ ለዐዳር በሰፈሩበት ቦታ ከእነርሱ አንዱ ለአህያው ጥሬ ለመስጠት ስልቻውን በፈታ ጊዜ በስልቻው አፍ ላይ ገንዘቡ ተቋጥሮ አገኘው።
ሉቃስ 10:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርሱም ቀርቦ ዘይትና የወይን ጠጅ በቊስሉ ላይ አፈሰሰ፤ በጨርቅም ጠምጥሞ አሠረለት፤ ከዚያም በኋላ በገዛ ራሱ አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ አንድ የእንግዶች ማደሪያ ቤት ወሰደው፤ በዚያም በልዩ ጥንቃቄ ተንከባከበው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀርቦም ቍስሎቹ ላይ ዘይትና የወይን ጠጅ አፍስሶ አሰረለት፤ በራሱም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማረፊያ ቤት ወሰደው፤ በዚያም ተንከባከበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቁስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፤ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደሪያ ወሰደው፤ ተንከባከበውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም ቀረበ፤ ቍስሉንም አጋጥሞ አሰረለት፤ በቍስሉ ላይም ወይንና ዘይት ጨመረለት፤ በአህያውም ላይ አስቀምጦ እንዲፈውሰው የእንግዶችን ቤት ወደሚጠብቀው ወሰደው፤ የሚድንበትንም ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀርቦም ዘይትና የወይ ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም። |
በመንገድ ላይ ሳሉ ለዐዳር በሰፈሩበት ቦታ ከእነርሱ አንዱ ለአህያው ጥሬ ለመስጠት ስልቻውን በፈታ ጊዜ በስልቻው አፍ ላይ ገንዘቡ ተቋጥሮ አገኘው።
በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለእንግዳ ማደሪያው ባለቤት ሰጠና ‘ይህን ሰው በጥንቃቄ አስታምልኝ፤ ተጨማሪ ወጪ ብታደርግም በምመለስበት ጊዜ እከፍልሃለሁ፤’ አለው።
በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።
ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ።