የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ዘሌዋውያን 8:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ ምግቡን ከእነርሱ ወሰደ፤ ስለ ክህነት ሹመት መባ እንዲሆን በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ላይ አድርጎ አቃጠለው፤ ይህም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ፣ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ መዐዛውም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ የቅድስና መሥዋዕት አድርጎ ሙሴ ከእጃቸው ተቀብሎ በሚቃጥለው መሥዋዕት ላይ በመሠዊያው አቃጠለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ በመሠዊያው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አኖረው። በጎ መዓዛ የቅድስና መሥዋዕት ነበረ። እርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ በመሠዊያው በሚቃጥለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው፤ የጣፋጭ ሽታ መቀደሻ ነበረ። እርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ከእነርሱም በመቀበል ለእኔ የምግብ መባ አድርገህ ታቀርበው ዘንድ በሚቃጠለው መሥዋዕት ጫፍ ላይ አኑረህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም መባ መዓዛው እኔን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
ያም ሰው የእንስሳውን ሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መሥዋዕቱን በሙሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።