ዘሌዋውያን 14:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ችሎታው በሚፈቅድለት መጠን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንዱን ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያመጣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ዐቅሙ የፈቀደውን አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመግዛትም አቅሙ የሚፈቅድለትን ያህል ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያደርገዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች በእጁ እንዳገኘ አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ይወስዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግልገሎች እንደሚቻለው፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ይወስዳል። |
አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤ እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ ድምፅሽ አስደሳች ነው፤ ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።
እንደ ሽመላ እጮኽ ነበር፤ እንደ ርግብ የሐዘን ድምፅ አሰማ ነበር፤ ወደ ሰማይም አሻቅቤ ከመመልከቴ የተነሣ፥ ዐይኖቼ በጣም ደክመው ነበር። ጌታ ሆይ! እባክህን ከዚህ ሁሉ መከራ አድነኝ!
ሁላችንም እንደ ድብ በመጮኽ እንደ ርግብም ምርር ብለን በማልቅስ ፍትሕንና መዳንን ለማግኘት እንጠባበቃለን፤ እነርሱ ግን ከእኛ የራቁ ስለ ሆኑ አይገኙም።
የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ።
“ሰውየው ይህን ሁሉ ለማምጣት የማይችል ድኻ ከሆነ፥ በመወዝወዝ ለኃጢአት ማስተስረያ ይሆንለት ዘንድ ለበደል መሥዋዕት የሚሆን አንድ ጠቦት ያምጣ፤ ከዚሁም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ለእህል መባ ያምጣ፤ እንዲሁም የሊትር ሲሶ የሆነ የወይራ ዘይት ያቅርብ፤
“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።