ኢያሱ 15:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻዕራይም፥ ዐዲታይም፥ ገዴራና ገዴሮታይም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፤ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቃርም፥ ጋዴርና ሰፈሮችዋ፥ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፥ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየፎከሩ እነርሱን በመከተል እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን የቅጽር በሮች ድረስ አሳደዱአቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ሬሳ እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን ድረስ ወደ ሻዕራይም በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ወደቀ።