ዮሐንስ 10:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ከአብ ዘንድ ብዙ መልካም ሥራዎችን አሳየኋችሁ፤ ታዲያ፥ የምትወግሩኝ ከእነዚህ ስለየትኛው ሥራ ነው?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ግን፣ “ከአብ የሆኑ ብዙ ታላላቅ ታምራትን አሳየኋችሁ፤ ታዲያ ከእነዚህ ስለ የትኛው ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ የትኛው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ በየትኛው ሥራ ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ፦ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው። |
ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።
እነርሱም “እኛ የምንወግርህ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ስለ መናገርህ ነው እንጂ ስለ መልካም ሥራህ አይደለም፤ ይኸውም አንተ ሰው ሆነህ ሳለ፥ ራስህን አምላክ ስላደረግህ ነው” ሲሉ መለሱለት።
እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የበለጠ ምስክር አለኝ፤ ምስክሬም አባቴ እንድሠራው የሰጠኝ ሥራ ነው፤ ይህም የምሠራው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራል።
“ደግሞም እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባውና ኀይልም እንደ ሰጠው ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ እርሱን መልካም ነገርን እያደረገና በዲያብሎስ የተያዙትን ሁሉ እየፈወሰ ተዘዋወረ።
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል አዳምጡ፤ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር በእናንተ መካከል በእርሱ አማካይነት በፈጸማቸው ታላላቅ ሥራዎች፥ ተአምራትና ምልክቶች ተረጋግጦአል።
የሰይጣን ወገን እንደ ነበረውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል መሆን አይገባንም፤ እርሱ ወንድሙን ስለምን ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ ስለ ነበረና የወንድሙ ሥራ ግን ትክክል ስለ ነበረ ነው።