ኢዮብ 41:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአፍንጫው መሰነጊያ አስገብተህ መንጋጋውንም በመንጠቆ ወግተህ ልትይዘው ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ ወይም ጕንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚከራከረኝና በሕይወት የሚኖርስ ማን ነው? ከሰማይ በታች ያለውም ሁሉ የእኔ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያንቀሳቅሰውም ዘንድ የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው? |
በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”