ለመሆኑ ብልኅ ሰው ምንም በማይጠቅሙ ቃላትና ዋጋ በሌለው ንግግር ይከራከራልን?
በማይረባ ቃል፣ ፍሬ ቢስ በሆነም ንግግር ይከራከራልን?
ከማይረባ ነገር፥ ወይስ ከማይጠቅም ንግግር ጋር ይዋቀሳልን?
ከከንቱ ነገር፥ ወይስ ከማይጠቅም ንግግር ጋር ይዋቀሳልን?
“በውኑ ብልኅ ሰው እንደ ነፋስ የማይጨበጥ ነገር ይናገራልን? በሆዱስ ጐጂ የሆነ ሐሳብ ሊኖረው ይገባልን?
አንተ እግዚአብሔርን መፍራት ትተሃል፤ ለእግዚአብሔር የሚገባውንም አምልኮ ታደናቅፋለህ።
ለእያንዳንዱ ሰው ተገቢውን መልስ መስጠት እንድታውቁ ዘወትር ንግግራችሁ ለዛና ጣዕም ያለው ይሁን።