በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።
ኤርምያስ 52:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር በዐሥረኛው ቀን የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ የሆነው ናቡዛርዳን ኢየሩሳሌም ገባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በዐምስተኛው ወር፤ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ባለሟል የክብር ዘበኞች አዛዥ የነበረው ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዓሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚያገለግለው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመተ መንግሥት በአምስተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በአሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የቆመው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። |
በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።
ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ናቡከደነፆር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፥ አምስተኛው ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ናቡዛርዳን ተብሎ የሚጠራው የናቡከደነፆር የክብሩ ዘበኞቹ አዛዥ ኢየሩሳሌም ገባ።
ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ይህን የሰማይ አምላክ በማስቈጣታቸው ምክንያት በከለዳውያን ሥርወ መንግሥት የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነው በናቡከደነፆር ጦር እንዲሸነፉ አደረገ፤ ቤተ መቅደሱ ፈራረሰ፤ ሕዝቡም ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ።
“ንጉሠ ነገሥቱ ለዘለዓለም ይኑር! የቀድሞ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆና ስትቀርና የቅጽሮችዋም በሮች በእሳት ሲወድሙ እንዴት አላዝንም?” ስል መለስኩለት።
እንዲሁም የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠበት ዘመንና፥ ከዚያም በኋላ የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ነግሦ ዐሥራ አንድ ዓመት እስከሆነው ድረስ ማለት በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ተወሰደ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል በኤርምያስ አማካይነት ተነግሮአል።
ይህችን ከተማ የከበቡ ባቢሎናውያን መጥተው ያቃጥሉአታል፤ እንደዚሁም እኔን ለማስቈጣት በጣራዎቻቸው ላይ ለባዓል ጣዖት ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትንና ለሌሎችም ጣዖቶች የመጠጥ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን ቤቶች ያቃጥላሉ።
በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን በከተማ የቀሩትን ሕዝብና ቀደም ብለው ወደ እርሱ ከድተው የገቡትንም ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በእስረኛነት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤
ውሳኔውን በሥራ ላይ እንዲያውል የተመደበው አርዮክ የተባለው የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ ስለዚህ ዳንኤል ወደ እርሱ ሄደና በዘዴ አነጋገር፦
“በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”