በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ንጉሡ ከእስራት ይፈታሃል፤ በደልህንም ይቅር ብሎ ወደ ቀድሞው ማዕርግህ ይመልስሃል፤ ቀድሞ የመጠጥ ቤት ኀላፊ ሆነህ ታደርገው እንደ ነበር የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።
ዘፍጥረት 40:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ጠጅ አሳላፊውን ወደ ቀድሞ ማዕርጉ መለሰው፤ ስለዚህ የወይን ጠጅ ጽዋውን ለንጉሡ መስጠት ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠጅ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ ሹመቱ መለሰው፤ ጽዋውንም በፈርዖን እጅ ሰጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠጅ አሳለፊዎቹንም አለቃ ወደ ስፍራው መለሰው ጽዋውንም በፈርዖን እጅ ሰጠ። |
በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ንጉሡ ከእስራት ይፈታሃል፤ በደልህንም ይቅር ብሎ ወደ ቀድሞው ማዕርግህ ይመልስሃል፤ ቀድሞ የመጠጥ ቤት ኀላፊ ሆነህ ታደርገው እንደ ነበር የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።
እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
አርጤክስስ በነገሠ በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር ከዕለታት በአንዱ ቀን ለንጉሠ ነገሥቱ የወይን ጠጅ አቀረብኩለት፤ ከዚያች ቀን በቀር ከዚህ ቀደም በፊቴ ላይ ምንም ዐይነት የሐዘን ምልክት አይቶብኝ አያውቅም ነበር።