ዘፍጥረት 38:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳ የዔርን ወንድም ኦናንን “ሂድና ወደ ወንድምህ ሚስት ገብተህ በደንቡ መሠረት ለወንድምህ መጠሪያ የሚሆን ዘር አስቀርለት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ይሁዳ አውናንን፣ “ዋርሳዋ እንደ መሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋራ ሩካቤ ሥጋ በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ይሁዳ አውናንን፥ “ዋርሳ እንደ መሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም አውናንን፥ “ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ፤ አግባትም፤ ለወንድምህም ዘርን አቁምለት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም አውናን፦ ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ አግባትም ለወንድምህም ዘርን አቁምለት አለው። |
ናዖሚም እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ! እባካችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋር ለመሄድ የምትፈልጉት ለምንድነው? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች እንደገና መውለድ የምችል ይመስላችኋልን?