ሁለቱም እንግዶች ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በዚህች ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ የልጆችህ እጮኛዎችና ሌሎች ዘመዶች ቢኖሩህ ከዚህች ከተማ በፍጥነት እንዲወጡ አድርግ፤
ዘፍጥረት 19:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ውጪ የነበሩት ወጣቶችና ሽማግሌዎች ሁሉ በሩን ማየት እንዳይችሉ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በሩን እንዳያገኙት በቤቱ ደጃፍ ላይ የተሰበሰቡትን ወጣቶችና ሽማግሌዎች ዐይን አሳወሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፥ ሰዎቹም ደጃፉን ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታለቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። |
ሁለቱም እንግዶች ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በዚህች ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ የልጆችህ እጮኛዎችና ሌሎች ዘመዶች ቢኖሩህ ከዚህች ከተማ በፍጥነት እንዲወጡ አድርግ፤
ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ።
ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል።
አሁንም እነሆ፥ የጌታ እጅ ይመታሃል፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ ለጥቂት ጊዜም የፀሐይን ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑ ዐይኖቹን ጭጋግና ጨለማ ሸፈናቸው፤ እጁን ይዞ የሚመራውንም ሰው ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ።