ዘፍጥረት 17:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አብርሃምን ካነጋገረው በኋላ ከእርሱ ተለይቶ ወደ ላይ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋራ መነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግግሩንም ከእርሱ ጋር በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ተለይቶ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ንግግሩን ከእርሱ ጋር በፈጸመ ጊዜ ከአብርሃም ተለይቶ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግግሩንም ከእርሱ ጋር በፈጸም ጊዜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ተለይቶ ወጣ። |
ነበልባሉ ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ ማኑሄና ሚስቱ እየተመለከቱ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ሆኖ ወደ ላይ ወጣ፤ እነርሱም በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።
የእግዚአብሔር መልአክ ቀረብ ብሎ በያዘው በትር ጫፍ ሥጋውንና እንጀራውን ነካ፤ እሳትም ከአለቱ ላይ ተነሥቶ ሥጋውንና እንጀራውን በላ፤ ከዚያም በኋላ መልአኩ ተሰወረ።