ዘፍጥረት 10:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አርዋዳውያን፥ ጸማራውያን፥ ሐማታውያን ነበሩ፤ ዘግይቶም የተለያዩት የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አርዋዳውያን፥ ጸማራውያን፥ ሐማታውያን ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓናውያን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራዲዎንን፥ ሰማርዮንን፥ አማቲንን ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኍላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። |
በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።
በዚህም ዐይነት የባቢሎን ሰዎች ሱኮትበኖት በተባለው አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ እንዲሁም የኩታ ሰዎች ኔርጋል ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም፥ ጣዖት ሠሩ፤ የሐማት ሕዝብ ኢሺማ ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም፤ ጣዖት ሠሩ፤
ከዚህ በኋላ አቢያ ኰረብታማ በሆነ በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ጸማራይም ተራራ ወጥቶ ቆመ፤ ድምፁን ከፍ በማድረግም ለኢዮርብዓምና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ አድምጡኝ!