ዘፀአት 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንዝ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ሁሉ ሞቱ፤ የዐባይ ወንዝ ውሃ ስለ ገማ ግብጻውያን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብጽ ምድር ደም የሌለበት ስፍራ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባይ ያሉት ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ከመከርፋቱ የተነሣ ግብጻውያኑ ውሃውን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብጽ ምድር ሁሉ ደም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓባይ ወንዝ የነበሩ ዓሦችም ሞቱ፤ የዓባይም ወንዝ ገማ፥ ግብጻውያንም ከዓባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉም፤ ደሙም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ አገር ሁሉ ነበረ። |
ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የወንዙን ውሃ መታው። የወንዙም ውሃ ተለውጦ ደም ሆነ፤
ከዚህ በኋላ የንጉሡ አስማተኞች በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ፤ ንጉሡም ልቡን በማደንደን ጸና፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ማዳመጥ እምቢ አለ።