ንጉሡም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ሙሴን ለማስገደል ፈለገ፤ ሙሴ ግን ኰብልሎ በዚያው ለመኖር ወደ ምድያም አገር ሄደ። እዚያም እንደ ደረሰ በውሃ ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤
ዘፀአት 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ገና በምድያም ሳለ እግዚአብሔር “ሊገድሉህ የሚፈልጉት ሁሉ ስለ ሞቱ ወደ ግብጽ ተመልሰህ ሂድ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በምድያም ሳለ እግዚአብሔር፣ “አንተን ሊገድሉህ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብጽ ሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን በምድያን፦ “ወደ ግብጽ ተመልሰህ ሂድ ነፍስህን የሚፈልጓት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ዘመንም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሞተ። እግዚአብሔርም ሙሴን በምድያም፥ “ነፍስህን የሚሹአት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብፅ ሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን በምድያም፥ “ነፍስህን የሚሹአት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና ተመልሰህ ወደ ግብፅ ሂድ፤” አለው። |
ንጉሡም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ሙሴን ለማስገደል ፈለገ፤ ሙሴ ግን ኰብልሎ በዚያው ለመኖር ወደ ምድያም አገር ሄደ። እዚያም እንደ ደረሰ በውሃ ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤
ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።