ዘፀአት 37:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክንፍ ያላቸውንም ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሠርቶ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሁለት ኪሩቤልን በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሁለት ኪሩቤል ሠራ፤ በስርየት መክደኛው ላይ በሁለቱ ጫፎች አደረጋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ኪሩቤልንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሠራ፤ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን አደረጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ኪሩቤልንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሠራ፤ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን አደረጋቸው። |
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
እግዚአብሔርም ቀጭን ሐር የለበሰውን ሰው “ከሕያዋን ፍጥረቶች በታች ባሉት መንኰራኲሮች መካከል አልፈህ ሂድ፤ ከከሰልም ፍም በእጅህ አፍሰህ ውሰድና በከተማይቱ ላይ በትነው!” አለው። እኔም እያየሁት ገባ፤