በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ የነቢዩንም ሬሳ አህያውና አንበሳው እስከ አሁን በአጠገቡ እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው። አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አልጣለበትም ነበር።
ዳንኤል 3:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ በሰጠው ጥብቅ ትእዛዝ መሠረት እሳቱ በኀይል ተቀጣጥሎ ይነድ ስለ ነበር ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብደናጎን ወደ እሳቱ የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን አቃጥሎ ገደላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡ ትእዛዝ አስቸኳይ ስለ ነበረና የእቶኑም እሳት እጅግ ስለ ነደደ፣ የእሳቱ ወላፈን ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን ወስደው የጣሏቸውን ወታደሮች ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው። |
በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ የነቢዩንም ሬሳ አህያውና አንበሳው እስከ አሁን በአጠገቡ እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው። አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አልጣለበትም ነበር።
አገሪቱን ለቀውላቸው እንዲወጡ ግብጻውያን ራሳቸውም ሕዝቡን በማጣደፍ “በአስቸኳይ ለቃችሁ ካልወጣችሁልን እነሆ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉአቸው።
በደጋግ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በክፉ ሰዎች ላይ ይደርሳል፤ በቀጥተኛ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በእምነተ ቢሶች ላይ ይመጣል።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
ሄሮድስም በበኩሉ ጴጥሮስን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ዘብ ጠባቂዎችን ከመረመረ በኋላ እንዲገደሉ አዘዘ፤ ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ሄዶ እዚያ ተቀመጠ።