የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ በግዛቱ ሥር ባሉት መንግሥታትና ሕዝቦች ጭምር እየተረዳ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ላይ የጦርነት አደጋ በሚጥልበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።
ዳንኤል 2:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎሃል፤ በሰው፥ በእንስሶችና በወፎች ላይ ሥልጣን ሰጥቶሃል፤ ስለዚህ የወርቁ ራስ አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ልጆችን፣ የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፤ በየትም ቦታ ቢሆኑ፣ በሁሉም ላይ ገዥ አድርጎሃል፤ እንግዲህ የወርቁ ራስ አንተ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚቀመጡበትም ስፍራ ሁሉ የሰው ልጆችንና የምድር አራዊትን የሰማይ ወፎችንም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፥ ለሁሉም ገዥ አድርጎሃል አንተ የወርቁ ራስ ነህ። |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ በግዛቱ ሥር ባሉት መንግሥታትና ሕዝቦች ጭምር እየተረዳ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ላይ የጦርነት አደጋ በሚጥልበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።
እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።
ከአንተ በኋላ በገናናነቱ የአንተን መንግሥት የሚያኽል አነስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዓለምን ሁሉ የሚገዛ በነሐስ የሚመሰል መንግሥት በሦስተኛ ደረጃ ይነሣል።
“እንግዲህ እኔ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አንተም ብልጣሶር ሆይ! ትርጒሙን ንገረኝ፤ በመንግሥቴ ያሉት ጠቢባን ትርጒሙን ሊነግሩኝ አይችሉም፤ አንተ ግን የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ ልትነግረኝ ትችላለህ።”
የመጀመሪያው አውሬ አንበሳ ይመስል ነበር፤ እርሱም እንደ ንስር ያሉ ክንፎች ነበሩት፤ እኔም እየተመለከትኩት ክንፎቹ ተነቃቀሉ፤ አውሬውም ቀና ብሎ እንደ ሰው በሁለት እግሮቹ ቆመ፤ ሰብአዊ አእምሮም ተሰጠው።