ዳንኤል 11:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣው ወሬ ያስደነግጠዋል፤ በታላቅ ቊጣ ተነሣሥቶ ብዙ ሰዎችን በማጥፋት እንዳልነበሩ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ያስደነግጠዋል፤ ብዙዎችንም ለማጥፋትና ለመደምሰስ በታላቅ ቍጣ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምሥራቅና ከሰሜን ግን ወሬ ያውከዋል፥ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቍጣ ይወጣል። |
ሮማውያን በመርከብ መጥተው ስለሚወጉት በብርቱ ይደነግጣል፤ ወደ ኋላውም አፈግፍጎ በታላቅ ቊጣ ለአይሁድ የተሰጠውን የተቀደሰ ቃል ኪዳን ያረክሳል፤ ተመልሶም ሃይማኖታቸውን ከካዱት ሰዎች ጋር ይወዳጃል።
በባሕሩና ቤተ መቅደሱ በተሠራበት ውብ ኮረብታ መካከል ባለው ስፍራ ታላላቅ ንጉሣዊ ድንኳኖችን ይተክላል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ በመጨረሻው ራሱ ይጠፋል፤ የሚረዳውም አያገኝም።”