በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!
ዳንኤል 11:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከተወሰነው ጊዜ በኋላ ግብጽን እንደገና ይወራል፤ ይሁን እንጂ እንደ በፊቱ አይሳካለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በተወሰነው ጊዜ ደቡቡን እንደ ገና ይወርራል፤ በዚህ ጊዜ ግን ውጤቱ ከበፊቱ የተለየ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተወሰነውም ጊዜ ይመለሳል ወደ ደቡብም ይመጣል፥ ነገር ግን ኋለኛው እንደ ፊተኛው አይሆንም። |
በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠለት፤ በራእዩም የተነገረው ቃል እውነት ነው፤ ነገር ግን ለማስተዋል እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ትርጒሙ በራእይ ተገለጠለት።
“ትልቅ የጦር ኀይል አደራጅቶ በድፍረት በግብጽ ንጉሥ ላይ ይዘምታል፤ የግብጽ ንጉሥም በበኩሉ እጅግ ታላቅ የሆነ የጦር ኀይል አዘጋጅቶ የመጣበትን ጦር ይመክታል፤ ነገር ግን የግብጹ ንጉሥ ሤራ ስለሚደረግበት አይሳካለትም።
የሶርያ ንጉሥ የማረከውን ሀብት ሁሉ ይዞ ይመለሳል፤ ልቡ ግን የተቀደሰውን ቃል ኪዳን ለማጥፋት ነው፤ የፈለገውን ሁሉ ካደረገ በኋላ ወደ አገሩ ይሄዳል።
ሮማውያን በመርከብ መጥተው ስለሚወጉት በብርቱ ይደነግጣል፤ ወደ ኋላውም አፈግፍጎ በታላቅ ቊጣ ለአይሁድ የተሰጠውን የተቀደሰ ቃል ኪዳን ያረክሳል፤ ተመልሶም ሃይማኖታቸውን ከካዱት ሰዎች ጋር ይወዳጃል።
እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።