ዳንኤል 11:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ትልቅ የጦር ኀይል አደራጅቶ በድፍረት በግብጽ ንጉሥ ላይ ይዘምታል፤ የግብጽ ንጉሥም በበኩሉ እጅግ ታላቅ የሆነ የጦር ኀይል አዘጋጅቶ የመጣበትን ጦር ይመክታል፤ ነገር ግን የግብጹ ንጉሥ ሤራ ስለሚደረግበት አይሳካለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ታላቅ ሰራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያነሣሣል፤ የደቡብ ንጉሥም ቍጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኀያል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ነገር ግን ከተዶለተበት ሤራ የተነሣ መቋቋም አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅም ሠራዊት ሆኖ ኃይሉንና ልቡን በደቡብ ንጉሥ ላይ ያስነሣል፥ የደቡብም ንጉሥ በታላቅና በብዙ ሠራዊት ሆኖ በሰልፍ ይዋጋል፥ ነገር ግን አሳብ በእርሱ ላይ ይፈጥራሉና አይጸናም። |
“የሶርያ ንጉሥ ወንዶች ልጆች ለጦርነት በመዘጋጀት ታላቅ ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ከእነርሱ አንዱ ጠራርጎ እንደሚወስድ እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ሆኖ በማለፍ በጠላት ምሽግ ላይ አደጋ ይጥላል።
እኔም አሁን የምነግርህ ነገር እውነት ነው።” ያም ሰው የሚመስለው መልአክ እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፦ “ሌሎች ሦስት ነገሥታት በፋርስ ላይ ይነግሣሉ፤ ከእነርሱ የሚከተለው አራተኛው ንጉሥ ከሌሎቹ ይልቅ በሀብት የከበረ ይሆናል፥ ከሀብቱም የተነሣ ኀይሉ በበረታ ጊዜ ሌሎቹን መንግሥታት በማስተባበር በግሪክ መንግሥት ላይ ይነሣል።
“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።
“የደቡብ ንጉሥ ማለትም የግብጽ ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከእርሱ ይልቅ የበረታ ሆኖ እጅግ ታላቅ ለሆነ መንግሥት መሪ ይሆናል።