ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ቈላስይስ 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሁሉ በሰው ሠራሽ ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ ሥራ ላይ ከዋሉ በኋላ ለመጥፋት የተወሰኑ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ ጠፊ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሁሉ ትእዛዛት በጥቅም ላይ በመዋላቸው የሚጠፉትን ነገሮች የሚጠቁሙ ናቸው፤ እንዲያው በቀላሉ የሰው ትእዛዛትና አስተምሮ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሁሉ እንደ ሰው ትእዛዝና ትምህርት ለጥፋት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት፦ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ንጉሡ የቀድሞ አባቶቹን አማልክት ያቃልላል፤ ሴቶች የሚወዱአቸውንም አማልክት ይንቃል፤ እርሱ ራሱን ከሁሉ በላይ አድርጎ ስለሚቈጥር አማልክትን ሁሉ ችላ ይላል።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
“ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ይሳደባሉ፤ እነርሱ ለመጠመድና ለመገደል እንደ ተወለዱ፥ በተፈጥሮ ስሜት እንደሚኖሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው፤ እንስሶች እንደሚጠፉ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።