ቈላስይስ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እርሱ በእግዚአብሔር መንፈስ እርስ በርሳችሁ መዋደዳችሁን ነግሮናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በመንፈስ ስላላችሁ ፍቅር ነገረን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም በመንፈስ ስለ ሆነው ስለ ፍቅራችሁ አስታወቀን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በመንፈስ መዋደዳችሁን ነገረን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በመንፈስ ስለሚሆን ስለ ፍቅራችሁ አስታወቀን። |
ወንድሞቼ ሆይ! ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ በትግሌ እንድትረዱኝ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።