ሐዋርያት ሥራ 7:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም እንዲህ አለው፦ ‘የቆምክበት ስፍራ የተቀደሰ ምድር ስለ ሆነ ጫማህን አውልቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታም እንዲህ አለው፤ ‘የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ስለ ሆነች ጫማውን ከእግርህ አውልቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ‘የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ ‘ጫማህን ከእግርህ አውልቅ፤ የቆምህባት ምድር የተቀደሰች ናትና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታም፦ ‘የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ። |
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትገባበት ጊዜ ለአረማመድህ ጥንቃቄ አድርግ፤ እዚያ ሄዶ ደጉን ከክፉ ለይተው የማያውቁ ሞኞች ሰዎች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ የምክር ቃላትን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ መገኘት ይበልጣል።
እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም።