ሐዋርያት ሥራ 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውኑ እግሩና ቊርጭምጭሚቱ በረታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውም እግሩና ቍርጭምጭሚቱ በረታ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጸና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ ያንጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ |
“እንግዲህ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? ይህ ታላቅ ተአምር በእነርሱ እጅ መደረጉ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ታውቆአል፤ ስለዚህ ልንክደው አንችልም።