በእሳት ትቃጠያለሽ ሕዝብሽም በጦርነት ማለቁ አይቀርም፥ በአንበጣ እንደ ተበላ ሰብል ትጠፊያለሽ፤ ስለዚህ እንደ አንበጣና እንደ ኲብኲባ ተባዙ።
2 ጢሞቴዎስ 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱ ንግግር እንደማይድን ቊስል ይቦረብራል፤ ከእነርሱም መካከል ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትምህርታቸው እንደማይሽር ቍስል ይሠራጫል፤ ከእነዚህም መካከል ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኛሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃላቸውም እንደ ቈላ ቊስል ይባላል፤ ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ከእነርሱ መካከል ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ናቸው፤ |
በእሳት ትቃጠያለሽ ሕዝብሽም በጦርነት ማለቁ አይቀርም፥ በአንበጣ እንደ ተበላ ሰብል ትጠፊያለሽ፤ ስለዚህ እንደ አንበጣና እንደ ኲብኲባ ተባዙ።
ከእነርሱ መካከል ሄሜኔዎስና እስክንድር ይገኛሉ፤ እነርሱ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ከመናገር መቈጠብን እንዲማሩ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁ።
ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ብዙ ሀብት አከማችታችኋል።