2 ሳሙኤል 22:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ከአፍንጫው ከሚወጣው የእስትንፋስ ወላፈንና በግሣጼው የባሕሩ ውስጥ ወለል ታየ፥ የምድሩም መሠረት ተገለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው ከሚወጣው፣ ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታየ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ተግሣጽ፥ ከአፍንጫው ከሚወጣው፥ ከእስትንፋሱ ቁጣ የተነሣ፥ የባሕር መተላለፊያዎች ታዩ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ተግሣፅ የተነሣ፥ ከመዓቱም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የባሕር ፈሳሾች ታዩ፤ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ዘለፋ፥ ከመዓቱም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የባሕር ፈሳሾች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ። |
እናንተ ተራራዎች! እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የሚያቀርበውን ወቀሳ ስሙ! እናንተም ጠንካራ የሆናችሁ የምድር መሠረቶች! አድምጡ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ይወቅሳል ይገሥጻልም።