በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”
2 ሳሙኤል 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ‘ወደ እኔ ቀርበህ ግደለኝ፤ በብርቱ ስለ ቈሰልኩ መሞቴ ነው!’ አለኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም፣ ‘እኔ በሞት ጣር ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ ‘እኔ የሞት ጣር ይዞኛል፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞኛልና ደግሞ እስካሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደለኝ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሰውነቴ ዝሎአልና፥ ደግሞ እስከ አሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያው ናትና በላዬ ቆመህ ግደለኝ አለኝ። |
በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”
እርሱም በዚህ ጊዜ ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ አረማውያን መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ይህን ለማድረግ እጅግ ስለ ፈራ አላደረገውም፤ ስለዚህም ሳኦል የራሱን ሰይፍ መዞ በመሬት ላይ በመትከል በላዩ ላይ ወደቀ፤
እርሱም የጦር መሣሪያ አንጋቹን ወጣት በፍጥነት በመጥራት፥ “ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ፤ ሴት ገደለችው እንድባል አልፈልግም” ሲል አዘዘው። ስለዚህ ወጣቱ በሰይፍ መትቶ ገደለው።
ጋሻጃግሬው የነበረውንም ወጣት “እነዚህ ያልተገረዙ እኔን ወግተው በመሳለቅ መጫወቻ እንዳያደርጉኝ አንተ ራስህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ፈርቶ አልገደለውም፤ ስለዚህም ሳኦል ራሱ የገዛ ሰይፉን ወስዶ በስለቱ ላይ ወደቀበት።