እኔ ከወደ ሰሜን የተባበሩ ሕዝቦች በባቢሎን ላይ እንዲዘምቱ አነሣሣለሁ፤ በእርስዋም ላይ አደጋ ይጥሉባታል፤ ከዚያም ትያዛለች፤ የእነርሱም ቀስቶች ተወርውረው ዒላማቸውን እንደማይስቱ እንደ ሠለጠኑ ወታደሮች ቀስቶች ናቸው።
2 ሳሙኤል 1:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮናታን ቀስት ሳይገድል የማይመለስ፥ የሳኦልም ሰይፍ ጠላትን የሚቈራርጥ ኀያላንን መትቶ የሚሰብር፥ ጠላትን የሚገድል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኀያላኑም ሥብ፣ የዮናታን ቀስት ተመልሳ አልመጣችም፤ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰችም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሞቱት ሰዎች ደም፥ ከኀያላኑም ሥብ፥ የዮናታን ቀስት ተመልሳ አልመጣችም፤ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰችም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሞቱት ደምና ከኀያላን ስብ፥ የዮናታን ቀስት ባዶዋን አልተመለሰችም፤ የሳኦልም ሰይፍ ባዶዋን አልተመለሰችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሞቱት ደምና ከኃያላን ስብ የዮናታን ቀስት አልተመለሰችም፥ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም። |
እኔ ከወደ ሰሜን የተባበሩ ሕዝቦች በባቢሎን ላይ እንዲዘምቱ አነሣሣለሁ፤ በእርስዋም ላይ አደጋ ይጥሉባታል፤ ከዚያም ትያዛለች፤ የእነርሱም ቀስቶች ተወርውረው ዒላማቸውን እንደማይስቱ እንደ ሠለጠኑ ወታደሮች ቀስቶች ናቸው።
ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤