2 ቆሮንቶስ 7:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ደስ ብሎኛል፤ የተደሰትኩበትም ምክንያት እናንተን ስላሳዘንኳችሁ ሳይሆን በሐዘናችሁ ምክንያት ንስሓ ገብታችሁ በመለወጣችሁ ነው፤ እንግዲህ ሐዘናችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነ እኛ ምንም አልበደልናችሁም ማለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን ደስ ብሎኛል፤ ደስታዬም ስላዘናችሁ ሳይሆን፣ ሐዘናችሁ ንስሓ ለመግባት ስላበቃችሁ ነው፤ ምክንያቱም ሐዘናችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከእኛ የተነሣ ምንም አልተጐዳችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን ሐዘናችሁ ወደ ንስሓ ስለመራችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ደስታዬ ስለ ሐዘናችሁ አይደለም፤ በማንኛውም መንገድ በእኛ በኩል እንድትጎዱ አንፈልግም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን እኔ ስለ እርሷ በብዙ ደስ ይለኛል፤ ደስታዬም ስለ አዘናችሁ አይደለም፤ ንስሓ ልትገቡ ስለ አዘናችሁ እንጂ፤ ከእናንተ አንዱ ስንኳ እንዳይጠፋ፥ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ አዝናችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና። |
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
ንስሓ መግባት ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ደጋግ ሰዎች ይልቅ ንስሓ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”
የምንመካበት ነገር ይህ ነው፤ ይህም እውነት መሆኑን ኅሊናችን ይመሰክርልናል፤ ከሌሎች ሰዎችና በተለይም ከእናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ባገኘነው ቅድስናና ቅንነት የተመሠረተ ነው፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር እንጂ በሰው ጥበብ አልነበረም።
ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁ መልእክት ያሳዘናችሁ ቢሆንም እንኳ መልእክቱን በመጻፌ አልጸጸትም፤ ተጸጽቼም ብሆን እንኳ የተጸጸትኩት መልእክቴ ለጥቂት ጊዜ ስላሳዘናችሁ ነው።