La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 27:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮአታም አባቱ እንዳደረገው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ሠራ፤ አባቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ዕጣን በማጠን ያደረገውን ኃጢአትም አልሠራም፤ ሕዝቡ ግን ኃጢአት መሥራቱን ቀጥሎ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን እንደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አልገባም። ሕዝቡም በበደሉ እንደ ገፋበት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ ጌታ መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አባ​ቱም ዖዝ​ያን እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ አል​ገ​ባም፤ ሕዝ​ቡም ገና ይበ​ድል ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 27:2
8 Referencias Cruzadas  

ዖዝያ የአባቱን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር አደረገ፤


አካዝ ዕድሜው ኻያ ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም ምሳሌነትን ባለመከተሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አላደረገም፤


አንተን ከመፍራቴ የተነሣ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርድህንም እጅግ ፈራሁት።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ ራሱን ስላረከሰ ፈጥነህ ውረድ፤


እናንተ ኃጢአተኞች በደልን የተሸከማችሁ ወገኖች! የክፉ አድራጊዎችም ትውልድ! ሕይወታችሁ የተበላሸ፥ እግዚአብሔርን የተዋችሁና የእስራኤልን ቅዱስ የናቃችሁ በእርሱም ላይ ጀርባችሁን ያዞራችሁ ናችሁ።


ከእነርሱ ውጪ ከሆኑት ሰዎች አንድ እንኳ ከእነርሱ ጋር ለመሆን የሚደፍር አልነበረም፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ ያከብራቸው ነበር።