2 ዜና መዋዕል 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ ኢዮአስ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያስኝ ነገር ያደርግ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ኢዮአስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በካህኑም በዮዳሄ ዘመን ሁሉ ኢዮአስ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአስም በካህኑ በኢዮአዳ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በካህኑም በዮዳሄ ዘመን ሁሉ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ። |
አሜስያስ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ያደርግ ነበር፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ የሚያደርገውን ነገር በሙሉ ልብ አያደርግም ነበር፤
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
“ነገር ግን ደግ ሰው መልካም ማድረጉን ትቶ ክፉ ሰዎች የሚያደርጉአቸውን ክፉና አጸያፊ ነገሮች ማድረግ ቢጀምር፥ በሕይወት መኖር የሚችል ይመስላችኋልን? አይደለም! እንዲያውም ያደረገው የደግነት ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ባለመታመኑና ኃጢአተኛም በመሆኑ ምክንያት ይሞታል።