ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዐይነት ርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?
1 ሳሙኤል 28:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ተለይቶህ ጠላትህ ከሆነ በኋላ እኔን ስለምን ታስጠራኛለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ታዲያ እግዚአብሔር ከራቀህ፣ ጠላትም ከሆነህ ለምን ትጠይቀኛለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ታዲያ ጌታ ከራቀህ፥ ጠላትም ከሆነህ ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም አለ፥ “እግዚአብሔር ከራቀህ፥ ወደ ባልንጀራህም ከተመለሰ ለምን ትጠይቀኛለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም አለ፦ እግዚአብሔር ከራቀህ ጠላትም ከሆነህ ለምን ትጠይቀኛለህ? |
ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዐይነት ርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?
እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ በቀኝ እጁ የያዘውን በእኛ ላይ አነጣጠረ፤ በኢየሩሳሌም ከተማ የምንመካባቸውን ሁሉ ገደለ፤ ቊጣውንም እንደ እሳት አቀጣጠለ።
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።
ሳሙኤልም ሳኦልን “ዕረፍት የምትነሣኝ ስለምንድን ነው? ስለምንስ ከመቃብር እንድነሣ አስጠራኸኝ?” አለው። ሳኦልም “እነሆ፥ እኔ በታላቅ ችግር ላይ ነኝ! ፍልስጥኤማውያን ከእኔ ጋር ጦርነት በማድረግ ላይ ናቸው፤ እግዚአብሔርም እኔን ትቶኛል፤ በነቢይም ሆነ በሕልም መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም፤ ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ትነግረኝ ዘንድ እንድትነሣ አስጠራሁህ” ሲል መለሰ።