1 ሳሙኤል 23:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ በዚህ እንዳለ ወዲያውኑ አንድ መልእክተኛ ደርሶ ሳኦልን “ፍልስጥኤማውያን አገሪቱን በመውረር ላይ ናቸውና አሁኑኑ ፈጥነህ ተመልሰህ ና!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሳኦልም መልእክተኛ መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ሀገሩን ወርረውታልና ፈጥነህ ና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሳኦልም መልእክተኛ መጥቶ፦ ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወርረውታልና ፈጥነህ ና አለው። |
በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦
ሳኦልና ወታደሮቹ ከኮረብታው በአንድ በኩል ሲሆኑ፥ ዳዊትና ተከታዮቹም ከኮረብታው በሌላ በኩል ነበሩ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ሊማርኩአቸው ከተቃረቡት ከሳኦልና ከወታደሮቹ ለማምለጥ በመጣደፍ ላይ ነበሩ።
ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው።
አኪሽ “በዚህ ጊዜ ወረራ ያደረጋችኹት በየት በኩል ነው” ብሎ ሲጠይቀው ዳዊት “እኛ የዘመትነው ከይሁዳ በስተ ደቡብ ባለው ክፍል፥ እንደገናም በይራሕመኤል ነገድ ግዛትና ቄናውያን በሚኖሩበት ግዛት ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።