La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 22:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልም “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ስለምንድን ነው? ለእርሱ ምግብና ሰይፍ ሰጥተኸዋል እግዚአብሔርንም ጠይቀህለታል፤ እነሆ፥ እርሱ አሁን በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶ እኔን ለመግደል አጋጣሚ ጊዜ በመፈለግ ላይ ነው” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦልም፤ “ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ፣ በእኔ ላይ እንዲያምፅብኝና እንዲያደባብኝ፣ እንጀራና ሰይፍ በመስጠት፣ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ በመጠየቅ ከእሴይ ልጅ ጋራ ለምን ዶለታችሁብኝ?” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦልም፤ “ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ፥ በእኔ ላይ እንዲያምፅብኝና እንዲያደባብኝ፥ እንጀራና ሰይፍ በመስጠት፥ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ በመጠየቅ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለታችሁብኝ?” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም፥ “አንተ ከእ​ሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለ​ት​ህ​ብኝ? እን​ጀ​ራና ሰይፍ ሰጠ​ኸው፤ ዛሬም እንደ ተደ​ረ​ገው ጠላት ሆኖ ይነ​ሣ​ብኝ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ እርሱ ጠየ​ቅ​ህ​ለት” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም፦ አንተና የእሴይ ልጅ ለምን ዶለታችሁብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፥ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት አለው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 22:13
5 Referencias Cruzadas  

ምንም እንኳ ትዕቢተኞች በሐሰት ስሜን ቢያጠፉ እኔ ትእዛዞችህን በሙሉ ልቤ እጠብቃለሁ።


የቤትኤል ካህን የሆነው አሜስያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ላከ፦ “እነሆ አሞጽ በእስራኤል ሕዝብ መካከል ሆኖ በአንተ ላይ እያሤረብህ ነው፤ ሕዝቡ የእርሱን ንግግር ሊታገሥ አይችልም።


ሳኦልም፥ “የአሒጡብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለው። አቤሜሌክም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” ብሎ መለሰ።


በእኔስ ላይ ሤራ የምታካሄዱት ስለዚህ ነውን? የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር መተባበሩን የነገረኝ ከእናንተ አንድ እንኳ የለም፤ ስለ እኔ የሚያስብ ከቶ ማንም የለም፤ ወይም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ አገልጋዬ በእኔ ላይ እንዲሸምቅ ልጄ ያነሣሣው መሆኑን ከእናንተ ማንም የነገረኝ የለም።”